በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቸነፈር ያበረራቸው የሶማሊያ ስደተኞች በዶሎ ኦዶ

በዶሎ ኦዶ የስደተኞች መጠለያ ሠፈር የሚገኙ የሶማሊያ ስደተኞች ሁኔታ እጅግ አሳሳቢ ሆኗል።

በረሃብ እጅግ የተጎዱ ህፃናት እና እናቶች በየሠፈሩ ይታያሉ። በቂ እርዳታ አላገኘንም የሚሉም አሉ። የመለስካቸው አምሃ ሪፖርት ይቀጥላል፡፡

ዶሎ ኦዶ ከተማ በደቡባዊ ምሥራቅ ኢትዮጵያ አገሪቱን ከሶማሊያ ጋር ከሚያገናኙ ትናንሽ ከተሞች አንዷ ናት። በዶሎ ኦዶ ከተማና በሶማሊያ ድንበር መካከል ያለው ልዩነት 2 ኪሎ ሜትር ነው።

የዓለም የምግብ ፕሮግራም ይህን የስደተኞች ጣቢያ ጥቂት ጋዜጠኞች እንዲጎበኙ ዕድሉን ሰጥቶ ነበረ። በደሎ አካባቢ ኃላፊ የሆኑት ሚስተር ጆ ፔገንሃወር ስለካምፖቹ አጀማመርና አሁን ስላሉበት ሁኔታ አጭር ገለፃ አድርገዋል።

ኮቤ ካምፕ የገናሌን ወንዝ ተጠግቶ የተመሠረተ ካምፕ ነው። የኮሚሽኑ ድንኳኖች በረድፍ የተደረደሩበት የኮቤ የስደተኞች ሠፈር አንድ አነስተኛ ከተማ ይመስላል። ለነገሩ ወደ 30 ሺህ የሚሆን ስደተኞች የሠፈሩበት የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ በመሆኑ እንጂ ለትንሽ ከተማነት በጭራሽ የሚያንስ አይደለም።

ካምፑ እንደደረስን ስደተኞቹ በሠልፍ ሆነው ወደ ተደረደሩበት አመራሁ። አብዱል መሃመድ እባላለሁ ያሉኝና ከበለዶይን አካባቢ እንደመጡ የነገሩኝን ስደተኛ በአስተርጓሚ አናገርኋቸው። ከሁለት ወር በፊት እንደመጡ ነገሩኝ። “በድርቅና በረብሻ ምክንያት ነው የመጣሁት” አሉ፡፡

ድርቁ ምን ያህል ጉዳት ቢያደርስባችሁ ነው ወደዚህ የመጣችሁት?

“ድርቁ በጣም ከፍተኛ ስለሆነ ፍየሎች፣ ከብቶችና ግመሎች ሁሉም አልቀዋል። የእርሻ ቦታ ነበረን አልሻባብ ከለከለን፤ ዝናብም ጠፋ ምንም ስለሌለን ወደዚህ መጣን።”

አልሻባብ ወደዚህ እንድትመጡ ፈቀደላችሁ?

“ይከለክላል። መምጣት አይፈቅዱም። ሴቶች ካየ ይነካል። ወንዶችን ካየ ያርዳል። እንድንመጣ አይፈቅዱም።”

ታዲያ እንዴት መጣችሁ?

“እንደሌባ በሌሊት በጫካ ውስጥ እየሄድን ነው የመጣነው። እንዲህ እያደረግን ስንመጣ እሱ ካየን ያርደናል።”

ወደዚህ ስትመጡ በምግብ ተጎድታችሁ ነበረ? እስኪ ሁኔታውን ይግለጹልን።

“መንገድ ላይ እያለን በምግብ ማጣት ሦስት ልጆች ሞተውብናል። የኔም ሦስት ልጆች በርሃብ ሞተዋል። እዚህ ከመጣን ምግብ አገኘን፤ ሰላም አገኘን።”

አብዱል መሃመድ እንዲህ ሲሉ ካጠገባችን የነበረ ሌላ ስደተኛ ጣልቃ ገባ። ወጣት ነው። እርሱንም ባስተርጓሚ አናገርኩት። መሃመድ ይባላል። ወደ ጣቢያውም በብዙ ችግር እንደደረሰበትና እዚህም ችግር እንዳጋጠመው ይናገራል።

“እዚህም ብዙ አስቸጋሪ ነገር አለ። የሚሰጠን ምግብ በጣም ትንሽ ነው። ከመጣሁ 45 ቀን ሆኖኛል፤ ምግቡ ግን በጣም ትንሽ ነው። ለኔ አይበቃኝም። በጣም ትንሽ ነው።”

ከኮቤ ካምፕ በ8 ኪ.ሜ. ርቆ የሚገኘው ሌላው ካምፕ መልከዲዳ የስደተኞች መጠለያ ነው። እዚህ ካምፕ ውስጥ ለመጎብኘት የታቀደው በምግብ እጦት እጅግ የተጎሳቆሉ ህፃናትና የሚያጠቡና ነፍሰጡር እናቶችን ነው። ካምፑ ውስጥ የተመለከትኩት ነገር እጅግ አስደንጋጭ ነው። ቆዳቸው ከአጥንታቸውጋር ተጣብቆ የመጨረሻ እስትንፋሳቸውን ለመተንፈስ የሚታገሉ የሚመስሉ ህጻናትን ማየት አሰቃቂ ነው። ለማነጋገርም ሆነ ፎቶ ለማንሳት አልተፈቀደልንም።

በዶሎኦዶ የመንግሥታቱ ድርጅት የስደተኞች ኮሚሽን ፅ/ቤት ኃላፊ ሚስተር ጆ ፔገንሃወር በስደተኞች ካምፕ የሚገኘውን ሰብዓዊ ቀውስ ባጭሩ ገልፀውታል።

“ሰብዓዊ ቀውሱ እጅግ ከፍተኛ ነው። በመላው ዓለም ተዘዋውሬ ስሠራ ብዙ ስደተኞችንና የስደተኞች ካምፕ አይቻለሁ። ችግሩ በጣም በጣም ከፍተኛ ነው ። እዚህ መመገቢያ ጣቢያ ውስጥ የምታያቸው ትንንሽ ልጆች በምግብ እጦት ማቀዋል። በጣም በሚያሳስብ ሁኔታ ላይ ነው ያሉት። ይህ ህዝብ እጅግ ተርቧል፤ ተዳክሟልም። ውኃና እርዳታ ያስፈልጋቸዋል። በጥቂት ቀናት ውስጥም የሚያገኙ ይመስለናል። በእርግጥ እርዳታ የሚያስፈልገው ህዝብ ነው።”

በአካባቢው ያለውን የዓለም የምግብ ፕሮግራም ሥራ አስተባባሪ አቶ ጌትነት አምሃ የችግሩን ክብደት ሳይረሱ ችግሩን ለማቃለል ልፋትና ረዘም ያለ ጊዜ እንደሚያሰፈልግ ይናገራሉ።

“ለነገሩ ይሄ ኑትሪሽን የሚባል ነገር በአንድ ጊዜ ቶሎ የሚቀረፍ ነገር አይደለም። አንድ ህጻን በመተመጣጠነ ምግብ ከተጎዳ ለማገገም ብዙ ነገር ይፈልጋል። ስለዚህ ነው ቶሎ የማያገግሙት። ብዙ ልፋትን ይጠይቃል። ለጋሾችም እየሰጡ ነው፤ ምግብም አለ። የዓለም የምንብ ፕሮግራምም ለለጋሾች ጥያቄ አቅርቧል። ጥያቄውም በተወሰነ መልኩ እየተመለሰ ነው።”

ከመልከዲዳ የተመለስነው ወደ ዶሎኦዶ ነው። ስንመለስ እየተጠማዘዘ ወደ ሶማሊያ የሚወርደውን ገናሌ ወንዝን እናየዋለን። ወንዙ ሙሉ ነው። ደግሞም በጣም ድፍርስ ነው። ሶማሊያውያን የሚራቡት ይህን ያህል የውጪ ወንዞች እየፈሰሱባት ነው። ይህም ያለውን ትርጉም አልባ ተቃርኖ ያሣያል።

ዘገባውን ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG