በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሶማልያ ክልል የገቡት ሶማልያውያን ስደተኞች ቁጥር ከተባለው 17,500 በላይ ስይሆን አልቀረም ተባለ


በጎዴ አከባቢ የገቡ ሶማልያውያን ስደተኞች ቁጥር ከ 17,000 በላይ ሊሆን እንደሚችል ተገለጸ። እስካሁን ባለው ጊዜ በቂ እርዳታ እንዳልተሰጣቸውና ይህም በአከባቢው ህበረተሰብ ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድር እንደሚችል ተገልጿል።

በተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኮሚሽን የኢትዮጵያ ጽህፈት ቤት ከፍተኛ የፓብሊክ ኢንፎርሜሽን ረዳት አቶ ክሱት ገብረእግዚአብሄር አዲስ ገቡ ስለተባሉት ሶማያውያን ብዘት ሲናገሩ " 17,500 አካባቢ ናቸው ተብሏል። ነገር ግን በየቀኑ ተጨማሪ ስደተኞች እየገቡ በመሆናቸው ቁጥሩ ከዛም በላይ ሊሆን ይችላል። አዲሶቹ ስደተኞች እስካሁን ባለው ጊዜ ምንም ያህል እርዳታ እያገኙ አይደሉም። ይህም በአከባቢው ህብረተሰብ የምግብ ዋስትና ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል" ብለዋል።

በሌላ በኩል ደግሞ በዶሎ ኦዶ የሰደተኛ ሰፈሮች የሚታየውን የህጻናት ሞት ለመቀነስ ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ እንደሆነ ተገልጿል።

XS
SM
MD
LG