በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሶማሊያ ፕሬዚዳንት የሞቃድሾ ከንቲባን አባረሩ


ኦማር ፊሊሽ
ኦማር ፊሊሽ

የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ መሃሙድ የሞቃድሾ ከንቲባ ኦማር ፊሊሽን ትናትን በጻፉት ደብዳቤ አባረሩ፡፡

ፕሬዚዳንቱ እምርጃውን የወሰዱት ባላፈው ወር እስላማዊ ታጣቂዎች ሆቴል ውስጥ የነበሩ 21 ሰዎችን በገደሉባት ሞቃድሾ፣ የራሳቸውንሰው መሾም ስለፈለጉ መሆኑን፣ አሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው ተንታኞች ተናግረዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ የሞቃድሾ ከንቲባና የባናዲር ክፍለ ግዛት ገዢ የሆኑትን ፊሊሽን ከሥልጣን ያሰናበቱት ከራሳቸው በቀጥታ በተላለፈ ደብዳቤ መሆኑ ተመልክቷል፡፡

ፕሬዚዳንቱ እምርጃውን የወሰዱት ከአገር ውስጥ ሚኒስቴር በቀረበላቸው ጥያቄ መሆኑን በደብዳቤያቸው አስታውቀዋል፡፡

ባሰናበቷቸው ፊሊሽ ምትክም ፕሬዚዳንቱ ዩስፍ ጃማኤልን በከንቲባነት ሾመዋል፡፡

ማዳሌ በሚል መጠሪያ የሚታወቁት ዩስፍ ጃማኤል ፕሬዚዳንቱ ሥልጣን ላይ በነበሩት ከ2007 እስከ 2009 ዓም ድረስ የሞቃድሾ ከንቲባ እንደነበሩ ተመልክቷል፡፡

ፕሬዚዳንቱ ከንቲባውን ስላባረሩበት ምክንያት ዝርዝር ማብራሪያ ባይሰጡም፣ ተንታኞች ግን “ፕሬዚዳንቱየሾሙት የራሳቸውን ለውጥና የደህንነት ፖሊሲ የሚቀበል ታማኝ ሰው ነው” ማለታቸውን የአሜሪካ ድምጽ የሶማልኛ ክፍል ዘጋቢ ሞሀመድ ዳኻይሴን ከሞቃድሾ የላከው ዘገባ ያስረዳል፡፡

XS
SM
MD
LG