በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሶማልያ ጠቅላይ ሚኒስትር ከስልጣን ተነሱ


Mogadishu
Mogadishu

የሶምልያ ምክር ቤት ዛሬ ሳይታሰብ ጠቅላይ ሚኒስትር ሐሰን ዐሊ ኻየርን የትምምን ድምጽ በመንፈግ ከስልጣን እንዳነሳቸው የምክር በቱ አፈ-ጉባይ ገልጸዋል።

አፈ-ጉባኤ ሞሐመድ ሙርሳል አብዱራሕማን የጠቅላይ ሚኒስትሩ መንግስት “ውጤታማ አይደልም” በሚል ነቅፈዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩን ከስልጣን ለማውረድ 170 የምክር ቤቱ አባላት ደግፈዋል። የተቃወሙት 8 ብቻ ናቸው ።

ስለሆነም ፕረዚዳንቱ አዲስ ጠቅላይ ሚኒስት እንዲሾሙ እንጠይቃለን ሲሉ አፈ ጉባኤው አስታውቀዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩና መንግስታቸው የተገቡትን ብሄራዊ ቃሎችን ለመተግበር አልቻሉም በማለት ነቅፈዋል።

XS
SM
MD
LG