በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአጎራባች የኦሮሚያና የሶማሌ ክልሎች ግጭት


በምሥራቅ ሐረርጌ ጭናቅሰን ወረዳ ውስጥ ለአራት ቀናት ውጊያ ሲካሄድ እንደነበር የአካባቢው ምንጮች ለቪኦኤ ገልፀዋል።

በምሥራቅ ሐረርጌ ጭናቅሰን ወረዳ ውስጥ ለአራት ቀናት ውጊያ ሲካሄድ እንደነበር የአካባቢው ምንጮች ለቪኦኤ ገልፀዋል።

ትናንት ካልማሌ፣ አምበሮ፣ ዋጩ፣ ለመፋ በተባሉ ቀበሌዎች ውስጥ ከጠዋቱ 11 ሰዓት አንስቶ ተኩስ መከፈቱና የአካባቢው ነዋሪም የመከላከል እርምጃ መውሰዱ ተነግሯል።

በሌላ በኩል ደግሞ የጉርሱም ወረዳ የፀጥታ ምክትል ኃላፊ የነበሩና አቶ መሐመድ አብዱራህማን የሚባሉ የቀድሞ አስተዳዳሪ አቶ ሰላን መሐመድ፣ እንዲሁም የኦሮምያ አድማ በታኝ ፖሊስ አባል የነበረ አብዱጀባር የሚባል ወጣት ወደ ሃረር እየተጓዙ ሣሉ ጥቃት አድራሾች ቦምባስ ከተማ ላይ ይዘዋቸው ያለፈውን ሌሊት እሥር ቤት ውስጥ ካሣደሯቸው በኋላ ሁለቱንም እንደገደሏቸው ተሰምቷል።

በተጨማሪም የጉርሱም ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ እንደነበረ የተነገረው አቶ መሐመድ አብዱልረሕማን ለማምለጥ ወደ ገደላማ ሥፍራ ሲዘልሉ ጉዳት ደርሶባቸው ሐረር ሆስፒታል ውስጥ እየታከሙ መሆኑ ተገልጿል።

በዚህም ምክንያት የጉርሱም ወረዳ ነዋሪ ዛሬ ጠዋት ከገጠርና ከከተማ ተሰባስቦ ሰልፍ የወጣ ሲሆን የኦሮምያ ፖሊስ ሰልፉን ለመበተን መተኮሱና የቆሰሉ ሰዎች መኖራቸው ተሰምቷል።

በኦሮምያና በሶማሌ ክልሎች አጎራባች አካባቢዎች እየታየ ያለው ጥቃትና ግጭት ከዕለት ወደ ዕለት እየሰፋ የመሆኑ ነገር ብዙዎችን እንዳሳሰበ ታውቋል።

በምሽቱ ዝግጅታችን ከሁለቱም ክልሎች ባለሥልጣናትና በጥቃቱ ውስጥ እጃቸው አለ ተብሎ ክስ ከተሰማባቸው ድርጅቶች የተሰጡ ምላሾች፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

በአጎራባች የኦሮሚያና የሶማሌ ክልሎች ግጭት
please wait

No media source currently available

0:00 0:32:43 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG