በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሶማሊያ የጦር ሰራዊት ሰባ የሚሆኑ የአልሻባብ ተዋጊዎችን መግደሉን ገለጸ


ፎቶ ፋይል - የሶማሊያ ብሔራዊ ጦር ወታደሮች
ፎቶ ፋይል - የሶማሊያ ብሔራዊ ጦር ወታደሮች

በሶማሊያ ደቡባዊ እና በማዕከላዊ ሶማሊያ ክፍለ ግዛቶች ባካሄድነው ጥቃት ስድሳ ዘጠኝ የአልሻባብ ታጣቂዎችን ገድለናል ሲሉ የሀገሪቱ ወታደራዊ ባለሥልጣናት አስታወቁ፡፡

የሶማሊያ የመከላከያ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ብርጌደር ጄኔራል አብዱላሂ አሊ አኖድ ትናንት ሐሙስ በሰጡት መግለጫ “ብሄራዊው የጦር ሰራዊት፣ የጎሳ ሚሊሽያ እና ዓለም አቀፍ አጋሮቻችን በመካከለኛው ሸበሌ ክፍለ ግዛት በህብረት ባደረሱት ጥቃት ቢያንስ 49 ታጣቂዎችን ገድለዋል መሳሪያዎችንም ማርከናል” ብለዋል፡፡

ባለፈው ማክሰኞ የአልሻባብ ታጣቂዎች ሞቃዲሾ አቅራቢያ የሚገኝ የጦር ሰፈር ላይ ጥቃት አድርሰው አንድ የሰራዊት አዛዥ ጨምሮ ቢያንስ 7 ወታደሮች እንደገደሉ ተዘግቧል፡፡

ጥቃቱ የደረሰው የሶማሊያ መንግሥት ሃራርዴሬን ጨምሮ ሽብርተኛው ቡድን ይዟቸው የነበሩ ስትራተጂያዊ የጠረፍ ከተሞች አስለቅቀን ታሪካዊ ድል ተቀዳጅተናል ባለ ማግሥት እንደነበር ይታወሳል፡፡

የሶማሊያ መንግሥት ኃይሎች ትናንት ሐሙስ ከባይዶዋ በስተሰሜን 30 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኝ አካባቢ በአልሻባብ ተዋጊዎች ምሽግ ላይ ባደረሱት ሌላ ጥቃት ደግሞ ቢያንስ ሃያ ታጣቂዎች መግደላቸውን የክፍለ ግዛቷ ባለሥልጣናት ተናግረዋል፡፡

XS
SM
MD
LG