ዋሺንግተን ዲሲ —
ለሥልጠና ወደኤርትራ የተላኩ የሶማሊያ ወታደሮች በሚስጥር በኢትዮጵያ የትግራይ ክልል በተካሄደው ውጊያ እንዲሳተፉ ተደርገዋል፤ ብዙዎችም ተገድለዋል መባሉን ተከትሎ የሶማሊያ ፕሬዚዳንት መሐመድ አብዱላሂ ፋርማጆ በጉዳዩ ዙሪያ ማብራሪያ እንዲሰጡ በሀገራቸው የምክር ቤት አባላት ተጠይቀዋል።
የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት ክሱን አስተባብሏል። መሐመድ ካሂዬ ከሞቃዲሾ ባጠናቀረው ዘገባ እንደገለጸው ሶማሊያውያኑ ወታደሮች በኢትዮጵያው ውጊያ ተሳትፈዋል፣ ቁጥራቸው ከሦስት መቶ ሰባ በላይ ሞተዋል፤ ያሉት አንድ የቀድሞ የሶማሊያ የብሄራዊ ደህንነት ምክትል ሃላፊ እና ወታደሮቹ ልጆቻችን ጠፍተውብናል ያሉ ወላጆች ናቸው። የሶማሊያም የኢትዮጵያም ባለሥልጣናት አስተባብለዋል።
ለዝርዝሩ ሙሉ ዘገባውን ከዚህ ያድምጡ።