በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሶማልያ የክልል ምክር ቤት አባል መገደላቸውን ፖሊስ አስታወቀ


ሶማልያ ውስጥ አንዲት የክልል ምክር ቤት አባል ትናንት ሞቃዲሾ ውስጥ በተጠርጣሪ አማፅያን መገደላቸውን ፖሊስ አስታወቀ።

ሶማልያ ውስጥ አንዲት የክልል ምክር ቤት አባል ትናንት ሞቃዲሾ ውስጥ በተጠርጣሪ አማፅያን መገደላቸውን ፖሊስ አስታወቀ።

ከፖሊስ በተገኘው መግለጫ መሠረት ሩቂያ አብሼረ ኖረ የተገደሉት፣ ሞቃዲሾ ውስጥ ሸቢስ ወረዳ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው አካባቢ ነው።

የግድያው ሪፖርት የደረሳቸው የጎረቤት ቦንድሄር ወረዳ የፖሊስ ኮማንደር አብዲዋቂ አብዱላሂ ለሞቃዲሾ ቪኦኤ እንደገለጹት፤ በተኩሱ ጽኑ ጉዳት የደረሰባቸው ኖረ ወደ ዋናው የሞቃዲሾ ሆስፒታል መዲና እንደተወሰዱ ነው ሕይወታችው ያለፈው፡፡

ኖረ የሶማልያ ፌዴራላዊ ግዛቶች አንዱ የሆነው የደቡባዊ ምዕራብ ክልላዊ ምክር ቤት አባል እንደነበሩም ታውቋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG