ዋሺንግተን ዲሲ —
ሶማሊያ ውስጥ ባለፈው ጥቅምት ወር "ቢያንስ አምስት መቶ ሰው ገድሏል፤ መኪና ላይ የተጫነ ቦምብ ጥቃት መርቷል" ተብሎ የተፈደበት ተከሳሽ በሀገሪቱ የጦር ፍርድ ቤት የሞት ቅጣት ተበይኖበታል።
ሃሳን ኢሳክ አደን የተባለው ተከሳሹ በዚያው ዕለት ሁለተኛ ጥቃት ለማድረስ የታቀደበትን መኪና ሲነዳ እንደነበር የጦር ፍርድ ቤቱ የመሃል ዳኛ ሃሰን አደን ሹታ ተናግረዋል።
ጠበቆቹ ይግባኝ ካላሉ የሞት ቅጣቱ በርሸና በአስቸኳይ ይፈፀማል ሲሉ ዳኛው አስታውቀዋል። ኢብራሂም ሃሰን አብሱጌ የተባለ ሊላ ሰውም ከቦምብ ጥቃቱ በተያያዘ በሌለበት የዕድሜ ልክ እስራት ተፈርዶበታል።
ሌሎች ሁለት ተጠርጣሪዎች ደግሞ ፍርድ ቤቱ በነፃ እንዲለቀቁ አዟል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ