በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሶማልያና የኤርትራ ፕሬዚዳንቶች በጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጡ

የሶማልያ ሞሐመድ ዐብዱላሂ ሞሐመድ /ፋርማጆ/ እና የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ
የሶማልያ ሞሐመድ ዐብዱላሂ ሞሐመድ /ፋርማጆ/ እና የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ

የሶማልያ ሞሐመድ ዐብዱላሂ ሞሐመድ /ፋርማጆ/ እና የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ፣ በሞቃዲሾ ለሁለት ቀናት ያደረጉትን የምክክር ስብሰባ ዛሬ ማጠናቀቃቸውን በጋራ ያወጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ያስረዳል።

የሶማልያ ሞሐመድ ዐብዱላሂ ሞሐመድ /ፋርማጆ/ እና የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ፣ በሞቃዲሾ ለሁለት ቀናት ያደረጉትን የምክክር ስብሰባ ዛሬ ማጠናቀቃቸውን በጋራ ያወጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ያስረዳል።

ሁለቱ ፕሬዚዳንቶች በቪላ ሶማልያ ባደረጉት ውይይት የንግድ ልውውጦችን ጨምሮ፣ በመዋዕለ ንዋይ ምደባና የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነቶችን የመሳሰሉ ታሪካዊ ግንኙነቶቻቸውን ለማጠናከር ተስማምተዋል።

በአፍሪካ ቀንድ የጋራ ልማት፣ እድገትና ብልፅግና ላይ ያተኮረ ትብብር ለመፍጠር ያላቸውን ቁርጠኝነትም ሁለቱ መሪዎች በድጋሚ አረጋግጠዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG