በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሂዩማን ራይትስ ዋች ስለሶማልያ መንግሥት


የሶማልያ መንግሥት ከአል ሸባብ ጋር ግንኙነት አላቸው በሚላቸው ልጆች ላይ በደል እያደረሰ ነው ሲል ሂዩማን ራይትስ የተባለው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ከሷል።

የሶማልያ መንግሥት ከአል ሸባብ ጋር ግንኙነት አላቸው በሚላቸው ልጆች ላይ በደል እያደረሰ ነው ሲል ሂዩማን ራይትስ የተባለው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ከሷል።

ድርጅቱ ዛሬ ባወጣው ዘገባ ወንዶች ልጆች ይታሰራሉ። አንዳንዴም በወታደራዊ ችሎት ይቀርባሉ ይልላ።

የሶማልያ ፌደራላዊ መንግሥት ልጆቹን ወደ ተባበሩት መንግሥታት ዓለምቀፍ የልጆች አስቸኳይ ጊዜ መልሶ የማቋቋሚያ አገልግሎት ለማስተላለፍ ቃል ገብቶ ነበር። ይሁንና ዓለምቀፍ የሰብዓዊ መብት ህግን የሚጥሱት ብሔራዊና ክልላዊ ባለሥልጣኖች ቋሚ የሆነ አሰራር እንዳላሳዩ ዘገባው አስገንዝቧል።

በሰብዓዊው መብት ድርጅት የአፍሪካ ጉዳይ ጥናት የሚያካሄዱትና የአሁኑን ዘገባ ያወጡት ነባር ሰራተኛ ሌትሻ ባደር እንደሚሉት የሶማልያ መንግሥት ባለፈው ጥር ወር 36 ልጆች ከአል ሸባብ ማርኳል። ልጆቹን ለመርዳት ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅትና ለልጆች መብት ከሚሟገት ድርጅት ጋር ለአንድ ሳማንት ያህል ቢደራደሩም የተወሰን ስኬት ብቻ ነው የተገኘው።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG