በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ በደረሰ ጥቃት የሞትና የመቁሰል አደጋ ደረሰ

ሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ በሚገኝ ሆቴል ዛሬ ማለዳ ላይ በደረሰ ጥቃት እስካሁን ከሃያ በላይ ሰዎች መገደላቸውና ሌሎች በርካቶች መቁሰላቸው ተዘገበ።

ሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ በሚገኝ ሆቴል ዛሬ ማለዳ ላይ በደረሰ ጥቃት እስካሁን ከሃያ በላይ ሰዎች መገደላቸውና ሌሎች በርካቶች መቁሰላቸው ተዘገበ።

በሁለት የዕቃ መጫኛ ካሚዮኖች ላይ የተጠመደ ቦምብ ከሞቃዲሾው የዳያህ ሆቴል ደጃፍ መፈንዳቱንና ተከትሎም ታጣቂዎች ወደ ሆቴሉ ገብተው ተገልጋይ እንግዶች ላይ ተኩስ መክፈታቸውን፣ ከፀጥታ ኃይሎች ጋርም መታኮሳቸውን የዓይን ዕማኞች ለአሜሪካ ድምፅ ገልጠዋል።

ካሁን ቀደም በሞቃዲሾ ሆቴሎችና ዋና ዋና ተቋማት ላይ በተደጋጋሚ ጥቃት የሚያደርሰው ጽንፈኛው እስላማዊ ቡድን አልሸባብ ለዛሬውም ጥቃት ኃላፊነት የሚወስድ መሆኑን ድረ ገጹ ላይ ባወጣው ፁሁፍ አመልክቷል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ በደረሰ ጥቃት የሞትና የመቁሰል አደጋ ደረሰ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:04 0:00

XS
SM
MD
LG