በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አልሻባብ በሶማልያ


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

የአልሻባብ ነውጠኛ ቡድን በተራራማው የሰሜን ምሥራቅ ሶማልያ ግዛት በባሪ ባሉ እስላማዊ መንግሥት ነን በሚሉ ተዋጊዎች ደጋፊዎች ላይ ጥቃት ማድረስ መጨመሩን ባለሞያዎች ይናገራሉ።

አልሻባብ ባለፈው ሣምንት ሁለት በእስላማዊ ነውጠኞች ቁጥጥር ሥር የነበሩ ይዞታዎችን አስለቅቆ ይዟል ሲሉ የሶማልያ የደኅንነትና የሴኩሪቲ ባለሥልጣናት ተናግረዋል።

አልሻባብ - እስላማዊ መንግሥት ነኝ ከሚለው ጽንፈኛ ቡድን ነውጠኞች ያስለቀቀው አንደኛው ይዞታ፣ ኤል-ሚራሌ ይባላል። ዋና የግጭቶች መነሻ ሊሆን የቻለው ውሃ በአካባቢው ስላለ መሆኑ ይዘገባል።

የእስላማዊ መንግሥት ነውጠኞች በአሁኑ ወቅት ወደ ተራራማው አካባቢ ቢያፈገፍጉም ግን ውጊያው አበቃ ማለት እንዳልሆነ ባለሞያዎች ያስረዳሉ።

በሁለቱ ወገኖች መካከል የተፈጠረውን ግጭት በቅርበት የሚከታተሉት የቀድሞው የፑንትላንድ የደኅንነት ጥበቃ ሹም አብዲ ሃሰን ሁሴን እንደሚያስረዱት፣ የአልሻባብና የእስላማዊ መንግሥት ነውጠኞች የሚዋጉት የዳኢሽ ዋና ምሽግ የሆኑትን ተራሮች ለመቆጣጠር ነው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የዩናይትድ ስቴትስ ጦር ሠራዊት ባለፈው አንድ ወር ጊዜ ዘጠኝ የአየር ድብደባዎችን በአልሻባብ ላይ ማካሄዱን ዛሬ አስታውቋል።

በ/AFRICOM/ መግለጫ መሠረት - ከትላንት በስቲያ በሂራን የሸበሌ መንደር ላይ በተካሄደ ጥቃት 24 የአልሻባብ ተዋጊዎች ተገድለዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG