በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአፋርና ሶማሌ የህዝብ ለህዝብ መድረክ


Afar - Somali
Afar - Somali

በሶማሌ ክልል የሲቲ ዞን የሃገር ሽማግሌዎችና አመራሮች ባለፈው ሳምንት የሰላም ሚኒስቴር ባዘጋጀው የአፋርና ሶማሌ የህዝብ ለህዝብ መድረክ ሶማሌዎች ተሳታፊ አልነበርንም ሲሉ ከሰሱ።

የሶማሌ ነዋሪዎች በሚበዙባት አና በአፋር ክልል ስር በምትገኘው አወዛጋቢዋ የአዳይቱ ወይም ገዳማይቱ ከተማ ላይ በተዘጋጀው መድረክ ላይ የፖለቲካ አመራሮችም፣ የኢሳ ጎሳ ኡጋዝም ሆነ የሃገር ሽማግሌዎች ተሳታፊ አልነበሩም፥ በተቃራኒው በዕለቱ በርካታ የኢሳ ሶማሌዎች ከተማዋን ለቅቀው እንዲወጡ መደረጋቸውንና የተወሰኑትም ታስረው እንደነበር አስታውቀዋል።

የሰላም ሚኒስቴር ግን መድረኩ በሁለቱ ክልሎች መካከል ሳይሆን አፋር ክልል ውስጥ ባሉ አፋሮችና ኢሳዎች መካከል የተዘጋጀ ነው ብሏል።

ኮንፈረንሱ የተካሄደባት የአዳይቱ ከተማ አፋርና ሶማሌ ክልል በይገባኛል ከሚወዛገቡባቸው ሶስቱ ቀበሌዎች አንዷ ነች።

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የአፋርና ሶማሌ የህዝብ ለህዝብ መድረክ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:36 0:00


የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG