በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የጂጂጋ ከተማ ነዋሪዎች አቤቱታ


ጂጂጋ ከተማ ከማኅበራዊ ሚዲያ ትዊተር ገፅ ላይ የተገኘ ፎቶ
ጂጂጋ ከተማ ከማኅበራዊ ሚዲያ ትዊተር ገፅ ላይ የተገኘ ፎቶ

በሶማሌ ክልል ጂጂጋ ከተማ የተፈጠረውን ግጭት ለማረጋጋት በክልሉ የተለያዩ ከተሞች የመከላከያ ሰራዊት እና የፌደራል ፖሊስ አባላት ከገቡ በኋላ የነበሩት ጥቃቶች ቆመው አንፃራዊ መረጋጋት ቢኖርም ከፍተኛ የሆነ የምግብና የመጠጥ ችግር መከሰቱን ነዋሪዎች ገለፁ።

በጂጂጋ ዩኒቨርስቲ የክረምት ትምሕርት ሲከታተሉ የነበሩ ተማሪዎችም ችግር ላይ መሆናቸውን ተናግርዋል። በሌላ በኩል በድሬደዋ ከተማ የደረሰውን ሞት ተከትሎ ጅቡቲ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ችግር እየደረሰባቸው መሆኑን በዛው የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሁንቤታውን ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በጂግጂጋና በሌሎች የሶማሌ ክልል ከተሞች የደረሰውን ችግር ለማርገብ እየሰራ መሆኑን ለሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን አስታውቋል።

የጂጂጋ ከተማ ነዋሪዎች አቤቱታ
please wait

No media source currently available

0:00 0:13:20 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG