በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በካቡል በአጥፍቶ ጠፊዎች ጥቃት የሰዎች ህይወት አለፈ


ታሊባን ዛሬ በአፍጋኒስታን መዲና ካቡል በመኪና በተጠመደ ፈንጂ የአጥፍቶ መጥፋት ጥቃት በማድረሱ ቢያንስ 10 ሰዎች ተገድለዋል።

የአፍጋኒስታን የሀገር አስተዳደር ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ናዝራት ራሂሚ በገለጹት መሰረት የሞቱት ሰዎች ሲቪሎች ናቸው። ካቡል በተፈጸመው ጥቃት 42 ሰዎች ቆስለዋል።

የአጥፍቶ መጥፋቱ ጥቃት የተፈጸመው ከፍተኛ ጥበቃ በሚደረግበት የዲፕሎማቶች መንደር ሲሆን የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲና ዋና ዋና የሀገሪቱ መንግሥት ተቋማትም ይገኙበታል።

የፍንዳታው ጥቃት ዒላማ ያደረገው ባዕዳንን ነው በማለት የታሊባን ቃል አቀባይ ለጥቃቱ ኃላፊነት ውስዷል።

የአማፅያኑ ቡድን ታሊባን በያዝነው ሳምንት የውጭ ሀገር ሰዎች በሚኖሩበት ጊቢ ላይ ባደረሰው ሌላ ጥቃት ቢያንስ 16 ሰዎች ሲገደሉ ከ 100 በላይ ቆስለዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG