በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኮንጎ የጦር አበጋዝ የዕድሜ ልክ እስራት ተፈረደበት


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

ኮንጎ ዲሞክራሲያዊት ሪፖብሊክ ውስጥ ብዛት ያላቸው የጦርነት ወንጀል አድራጎቶች በመፈፀም የተወነጀለ የጦር አበጋዝ በሀገሪቱ ፍርድ ቤት የዕድሜ ልክ እስራት ተፈርዶበታል።

ኮኮዲኮኮ በሚል ቅፅል ስም የሚታወቀው ፍሬዴሪክ ማሱዲ አሊማሲ አስገድዶ በመድፈር መርዝ በመመረዝ በማሰቃየት በመግደል እና በወሲብ ባርነት በመያዝ ወንጀሎች ጥፋተኛ ሆኖ ተገኝቱዋል።

አንዲት የአስር ዓመት ልጅን ጨምሮ የተለያዩ ሰለባዎች የአሊማሲ ሚሊሽያ አባላት እንደደፈረዋቸው ለፍርድ ቤቱ ቃላቸውን ሰጥተዋል። ፍርድ ቤቱ ሊሎች ሁለት የሚሊሽያው አባላት የጥፋተኝነት ብይን የሰጠ ሲሆን ሌሎች ሁለት ደግሞ በነፃ ተለቀዋል።

የኮንጎው ፍርድ ቤት በተጨማሪም የሀገሪቱ መንግሥት ሰለባዎቹን ከጥቃት ባለመጠበቁ ካሳ እንዲከፍላቸው አዟል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG