በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሀገር ውስጥ ምርቶች ተፈላጊነት መጨመር በጥራታቸው መሻሻል ወይስ በዋጋቸው?


የሀገር ውስጥ ምርቶች ተፈላጊነት መጨመር በጥራታቸው መሻሻል ወይስ በዋጋቸው?
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:12 0:00

የሀገር ውስጥ ምርቶች ተፈላጊነት መጨመር በጥራታቸው መሻሻል ወይስ በዋጋቸው?

በኢትዮጵያ በየጊዜው እየጨመረ ባለው የኑሮ ውድነት የተነሣ፣ ማኅበረሰቡ የግብይት ትኩረቱን ወደ ሀገር ውስጥ ምርቶች እያዞረ እንደኾነ፣ የአሜሪካ ድምፅ ያናገራቸው ነጋዴዎች እና ባለሞያዎች ገልጸዋል፡፡

የሚበዙት የሀገር ውስጥ ምርቶች፣ በዋጋቸው ተመጣጣኝ እንደኾኑ አስተያየት ሰጪዎቹ ቢጠቅሱም፣ አንዳንዶቹ ግን፣ ከውጭ ከሚገቡት ምርቶች በላይ ውድ እንደኾኑ፣ የፋይናንስ ባለሞያው አቶ ሚሊዮን ክብረት ያስረዳሉ፡፡

በወጪ እና ገቢ ንግድ ላይ የተሰማሩት አቶ ጥላሁን ጫላ ደግሞ፣ የሀገር ውስጥ ምርቶቹን ተመራጭ ያደረጋቸው፣ በጥራታቸው እያደጉ መምጣታቸው እንደኾነ ያስረዳሉ፡፡ ይኹንና፣ በመጠናቸው በቂ እንዳልኾኑ ተናግረዋል፡፡

በጉዳዩ ላይ፣ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሓላፊዎችን ለማነጋገር ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG