በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በመንገድ ሥራ ምክንያት ማሳቸው ላይ የተቆለለ አሸዋና ጠጠር ለችግር እንደዳረጋቸው ገበሬዎች ገለጹ


ደቡብ ክልል፥ በጋሞ ጋፋ ዞን፥ የደምባ ጎፋ ወረዳ የሱካና የጉራደ ቀበሌ የሚኖሩ አርሶ አደሮች በመሬት ግንባታ ምክኒያት የእርሻ መሬታቸው ካመረቱት ሰብል ጋር መውደሙን፣ መሬቱ ላይ አሸዋና ጠጠር ተቆልሎ
ደቡብ ክልል፥ በጋሞ ጋፋ ዞን፥ የደምባ ጎፋ ወረዳ የሱካና የጉራደ ቀበሌ የሚኖሩ አርሶ አደሮች በመሬት ግንባታ ምክኒያት የእርሻ መሬታቸው ካመረቱት ሰብል ጋር መውደሙን፣ መሬቱ ላይ አሸዋና ጠጠር ተቆልሎ

ደቡብ ክልል፥ በጋሞ ጋፋ ዞን፥ የደምባ ጎፋ ወረዳ የሱካና የጉራደ ቀበሌ የሚኖሩ 38 አርሶ አደሮች በመሬት ግንባታ ምክኒያት የእርሻ መሬታቸው ካመረቱት ሰብል ጋር መውደሙን፣ መሬቱ ላይ አሸዋና ጠጠር ተቆልሎ አራት ዓመታት መቆጠሩን አርሶ አደሮቾ ይናገራሉ። ከዚህ በኋላ ማረስ እንዳልቻሉ፣ ልጆቻቸውን ማስተማርና ቤተሰቦቻቸውን መመገብ እንደተሳናቸውም በምሬት ይናገራሉ።

በደቡብ ክልል፥ በጋሞ ጋፋ ዞን፥ የደምባ ጎፋ ወረዳ የሱካና የጉራደ ቀበሌ የሚኖሩ 38 አርሶ አደሮች በመንገድ ሥራ ምክንያት ከመሬታቸው መፈናቀላቸው፣የእርሻ መሬታቸው ከነ እርሻ ሰብሉ መውደሙን፣ መሬቱ ላይ አሸዋና ጠጠር ተቆልሎ ከዚህ በኋላ ማረስ እንዳልቻሉ፣ ልጆቻቸውን ማስተማርና ቤተሰቦቻቸውን መመገብ እንደተሳናቸው ገለጹ። ይህንን አቤቱታ ለአራት ዓመታት ለሚመለከተው አካል ቢያቀርቡም እስካሁን ምላሽ እንዳላገኙ ገልፀው ከሥራቸው ተፈናቅለው ለጎዳና ሊዳረጉ መሆኑን ተናግረዋል።

በመንገድ ሥራ ምክንያት ማሳቸው ላይ የተቆለለ አሸዋና ጠጠር ለችግር እንደዳረጋቸው ገበሬዎች ገለጹ
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:36 0:00

ከፌደራል መንገዶች ባለሥልጣንና የተጠቀሰው አቤቱታ እንደቀረበለትና አጥኒ ቡድን ልኮ ጉዳቱ ትክክለኛ መሆኑን እንዳረጋገጠ ገልፆ በቀጣይ ካሳ እንደሚከፈል አስታውቋል።

አርሶ አደሮቹ በበኩላቸው እንዲህ ዓይነት ምላሽ ከዚህ ቀደም ማግኘታቸውን ነገር ግን በወረዳውም ሆኑ በክልሉ በኩል ምንም የተደረገላቸው ነገር እንደሌለ ተናግረዋል።

ጽዮን ግርማ ዝርዝር አላት።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ይከታተሉ።

በመንገድ ሥራ ምክኒያት ማሳቸው ላይ የተቆለለ አሸዋና ጠጠር ለችግር እንደዳረጋቸው ገበሬዎች ገለጹ
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:36 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG