በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የእሥራኤል ጦር በመላ ጋዛ የአየር ድብደባ አካሂዷል


የእሥራኤል ድብደባ የተከተለው ሠርጡ ውስጥ የሚገኙ ፍልስጥዔማዊያን ታጣቂዎች በመቶዎች የሚቆጠሩ ሮኬቶችን ካዘነቡ በኋላ መሆኑ ተዘግቧል።

በጥቃቱና በአፀፋው ቢያንስ ስምንት ፍልስጥዔማዊያንና ሦስት እሥራኤላዊያን መገደላቸው ታውቋል።

እሥራኤል ድብደባውን ያካሄደችው በሃማስና በእስላማዊ ጂሃድ ዒላማዎች ላይ መሆኑም ተገልጿል።

የእሥራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ቁጥራቸው በርከት ያለ ወታደሮች በጋዛ አዋሣኝ አካባቢዎች ላይ እንዲሰፍሩ ያዘዙ ሲሆን ይህ እርምጃ ምናልባት የእግር ወረራ ሳያካሂዱ አይቀሩም የሚል ጥርጣሬን ቀስቅሷል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG