በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሲአን መግለጫ


ሲአን
ሲአን

ሥርዓቱ በህገ መንግሥታዊ ጉዳዮች ጣልቃ መግባቱ የለውጡን አካሄድ ጥያቄ ውስጥ እያስገባ ስለመሆኑ ማሳያ ነው አለ የሲዳማ አርነት ንቅናቄ /ሲአን/፡፡

ሲአን በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ምርጫ ኮሚሽን ውሳኔ ህዝብ ለማስፈፀም ዝግጁ አለመሆኑን ተቃውሟል፡፡ የብሄራዊ ምርጫ ኮሚሽን ምላሽ ለማግኘት ከትናንት ጀምሮ ያደረግነው ሙከራ አልተሳከም፡፡

ፖለቲካዊ ጣልቃ ገብነት አሳይቷል ተብሎ ድርጅቱ የወቀሰው የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ዴኢህዴን/ ጥያቄው ኃላፊነት በተሞላበት መንገድ እንዲፈታ ተወያይቷል ጣልቃ ገባ የሚባልበት ምክንያት የለም ይላል፡፡

የህዝብና ቤት ቆጠራ በተመለከተም ማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ በሀዋሳና በሲዳማ ዞን ሲከተለው የነበረውና ሀዋሳን ከሲዳማ ውጭ የማድረግ አዝማሚያ አጥብቆ እንደሚቃወምና የዕርምት ዕርምጃ እንዲወሰድ ጠይቋል፡፡

ያለፈውን ቆጠራ ወጤት የኛ ብቻ ሳይሆን የሁሉም ባለድርሻ አካላት የሥራ ውጤት ነው የሚለው ብሄራዊ ፕላን ኮምሽን ማዕከላዊ ስታቲክስ ኤጄንሲ የሀዋሳ ቅርንጫፍ ባለፈው ላይ ከመነታረክ ይልቅ የዚህን ዙር ቆጠራ ለማሳካት ሁሉም መረባረብ አለበት ብሏል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ

የሲአን መግለጫ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:25 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG