በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከጅቡቲ የባህር ዳርቻ በደረሰ የጀልባ መገልበጥ አደጋ የበርካታ ሰዎች ሕይወት ጠፋ


የጅቡቲ ካርታ
የጅቡቲ ካርታ

77 ሰዎችን አሳፍራ ስትጓዝ የነበረች ጀልባ ከጅቡቲ የባህር ዳርቻ ተገልብጣ 16 ለህልፈት ሲዳረጉ፣ ሌሎች 28 ሰዎች ደግሞ እስካሁን ያለመገኘታቸውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ቢሮ ዛሬ አስታወቀ።

ይህን መሰል አደጋ በሁለት ሳምንታት ውስጥ ሲደርስ ያሁኑ ሁለተኛው መሆኑን ያስታወሰው ዓለም አቀፉ የፍልሰት - አይኦኤም ‘ኤክስ’ በተሰኘው የማኅበራዊ ትስስር ገጽ ላይ ባሰፈረው ጽሑፍ በጀልባዋ ተሳፍረው ከነበሩት ውስጥ ህጻናትም እንደሚገኙበት አክሎ አመልክቷል። የጅቡቲ ቢሮው በነፍስ አድን ጥረቱ እያገዘ መሆኑንም አይኦኤም አስታውቋል።

የጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በበኩሉ ጉዳዩን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ጀልባዋ የተገለበጠችው ትላንት አመሻሽ ላይ መሆኑን ጠቁሟል።

ከሁለት ሳምንት በፊት ከጅቡቲ የባህር ዳርቻ በአንዲት ጀልባ ላይ የደረሰ ሌላ አደጋ ህጻናትን ጨምሮ 38 ሰዎች መሞታቸው ይታወሳል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG