በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ደብረ ታቦርና ዱር ቤቴ ላይ ሕይወት መጥፋቱን መኢአድ አስታወቀ


በአማራ ክልል በደብረ ታቦር ከተማና ዱር ቤቴ ላይ በተፈጠሩ ግጭቶች የስድስት ሰው ሕይወት መጥፋቱን የመላ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት - መኢአድ አስታውቋል፡፡

ደብረ ታቦርና ዱር ቤቴ ላይ ሕይወት መጥፋቱን መኢአድ አስታወቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:56 0:00

በአማራ ክልል ሥራ የማቆም አድማ መመታቱን፣ ደብረ ታቦር ከተማ ላይ ሦስት ሰው፤ እንዲሁም ዱር ቤቴ ሦስት ሰው በተፈጠሩ ግጭቶች መገደላቸውን፣ በአካልና በሕይወት ላይም ጉዳት መድረሱን የመላ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት - መኢአድ አስታውቋል፡፡

የመኢአድ ዋና ፀሐፊ አቶ አዳነ ጥላሁን ለቪኦኤ በሰጡት ማብራሪያ በክልሉ በርካታ ከተሞች ውስጥ ሰላማዊ ሰልፎች መደረጋቸውን፤ የሥራ ማቆም አድማዎች መመታታቸውን ገልፀዋል፡፡

ጎንደር ላይ አድማው ዛሬም ቀጥሎ መዋሉንና ደምበጫ ላይ ወደ ደብረ ማርቆስ የሚወስድ መንገድ መዘጋቱን፣ በቋሪት ወረዳ አዴት ከተማ በማቻከል ወረዳ፣ በሞጣ፣ በጋይንት፣ በአዲስ ዘመን፣ በአርባያና በሌሎችም አካባቢዎች የተለያዩ እንቅስቃሴዎች መኖራቸውንና ውጥረት መኖሩን አቶ አዳነ ዘርዝረዋል፡፡

አቶ አዳነ በተጨማሪም ባስተላለፉት መልዕክት “በዚህ ሕዝባዊ እምቢተኝነት የሚሣተፉ ሕዝቦች ሁሉ የትግራይ ሕዝብ ወገናችን፣ አጋራችን፣ ከእኛ በበለጠ ተጎጂ እንጂ ከእኛ ባላነሠ ተጠቃሚ አለመሆኑን፣ በወያኔ/ኢሕአዴግ የሚረገጥ ሕዝብ መሆኑን ሕዝቡ በመገንዘብ የፖለቲካ ሥራ በፀዳ መልኩ በሚገኙ የትግራይ ተወላጆች ዙሪያ የተሣሣተ እርምጃ እንዳይወስድ እንደ አንድ ግለሰብ አደራዬን ለማስተላለፍ እፈልጋለሁ፤ ጥሪዬን ማቅረብ እፈልጋለሁ” ብለዋል፡፡

ስለዛሬ የአማራ ክልል ውሎ በተለያየ ደረጃ ከሚገኙ የክልሉ ባለሥልጣናት ማብራሪያ ለማግኘት የተደረጉ ተደጋጋሚ ጥረቶች አልተሣኩም፡፡

ለተጨማሪና ዝርዝር መረጃ ከዚህ ዘገባ ጋር የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG