ዋሺንግተን ዲሲ —
አምስት የደቡብ አፍሪካ ፖሊስ መኮንኖችና አንድ በግዳጅ ሥራ ላይ ያልነበረ ወታደር ዛሬ ገጠር በሚገኝ የፖሊስ ጣቢያ ላይ በተከፈተ ጥቃት ተገድለዋል።
አንድ የፖሊስ ቃል አቀባይ በገለፀው መሰረት የፖሊስ መኮንኖቹ የተገደሉት ታጣቂዎች ኢንግኮቦ በተባለው ደቡባዊ መንደር በሚገኘው የፖሊስ ጣብያ ላይ ሌሊቱን ባደረሱት ጥቃት ነው። አጥቂዎቹ መሳርያዎች ዘርፈው፣ ሁለት ሌሎች ፖሊሶችን ጠልፈው በፖሊስ መኪና አምልጠዋል። ወታደሩ የተገደለው ታጣቂዎቹ ያመልጡ በነበረበት ወቅት ነው።
የተጠለፉት ሁለት ፖሊሶች አስከሬን መንገድ ላይ ተጥሎ ተገኝቷል። የፖሊስ ሚኒስትር ፊኪሌ ምቡላላ የደረሰው ጥቃት “ብሄራዊ ሀዘንና ጉዳት ነው” ብለዋል። ደቡብ አፍሪካ በዓለም ደረጃ ከፍተኛ ወንጀል ከሚፈጸምባቸው ሀገሮች አንዷ ነች።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ