በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአወዳይ ከተማ በመንግሥት ታጣቂዎችና ሕዝብ መሃል በተፈጠረ ግጭት ስድስት ሰዎች ሞቱ


በምሥራቅ ሐረርጌ ዞን አወዳይ ከተማ ዛሬ በተፈጠረው ግጭት ስድስት ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል።

የሀሮምያ ሆስፒታል በበኩሉ የተገደሉት ሰዎች ቁጥር አራት መሆኑን ጠቅሶ በአሁኑ ወቅት በሆስፒታሉ ውስጥ ህክምና በማግኘት ላይ ያሉት ሶስት መሆናቸውን አረጋግጧል።

በአወዳይ ከተማ ውስጥ ያለ አንድ የሞባይል ስልክ መሸጫ ሱቅና አጠገቡ ያለው የፍራሽ መሸጫ ሱቅ ባልታወቀ ምክንያት በመቃጠላቸው የተነሣ የአከባቢው ህዝብ እሳቱን ለማጥፋት ጥረት ቢያደርግም ሊሳካ ባለመቻሉ በአከባቢው ያሉትን የኦፒዲኦ ባለሥልጣናት ለእርዳታ ቢማፀኑም ቆመው ከመሳቅ ባለፈ ምንም እርዳታ ባለማድረጋቸው የተበሳጩ ነዋሪዎች “ድሮም እናንተ የምታደርጉልን ነገር የለም” ስለዚህ ከዚህ ሂዱ ብለው በመናገራቸው የፀጥታ ሀይሎች በስልክ ወደ ቦታው መጠራታቸውን ግጭቱ መከሰቱን መሃመድ አባ ገሮ የተባለ ወጣት ለአሜሪካ ድምፅ ኦሮምኛ ክፍል ገልጿል።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ድምፅ ያድምጡ።

በአወዳይ ከተማ በመንግሥት ታጣቂዎችና ሕዝብ መሃል በተፈጠረ ግጭት ስድስት ሰዎች ሞቱ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:51 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG