በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሱዳን እና ደቡብ ሱዳን አወዛጋቢ ድንበር ላይ ስድስት ሰዎች ተገደሉ


በሱዳን እና ደቡብ ሱዳን የይገባኛል ውዝግብ በሚነሳበት አቢዬ ክልል፣ አንድ የአካባቢውን አስተዳዳሪ ጨምሮ ስድስት ሰዎች በታጣቂዎች መገደላቸውን ባለስልጣናት አስታወቁ።

ከፍተኛ የነዳጅ ሀብት በሚገኝበት የአቢዬ አካባቢ፣ የሱዳን እና የደቡብ ሱዳን ተቀናቃኛ የዲንቃ ብሄረሰቦች በሚያነሱት የአስተዳደር ወሰን ውዝግብ ምክንያት ተደጋጋሚ ሁከት ይከሰታል።

የክልሉ ምክትል አስተዳዳሪ ኑን ዴንግ እና የስራ ባልደረቦቻቸው ጥቃት የደረሰባቸው፣ የፈረንጆቹን አዲስ አመት አክብረው በመመለስ ላይ እንዳሉ መሆኑን የመንግስት ባለስልጣናት ተናግረዋል። ለጥቃቱም በደቡብ ሱዳን የሚገኙትን ትዊክ የዲንቃ ብሄረሰብ አባላትን ተጠያቂ አድርገዋል።

በህዳር ወር ላይም በክልሉ በተፈጠረ የብሄር ግጭት ምክንያት በደርዘን የሚቆጠሩ ሰዎች ተገድለው ነበር።

እ.አ.አ በ2011 ጁባ ከካርቱም ነፃነቷን ስታውጅ፣ በደቡብ ሱዳን እና በሱዳን መካከል ያለው ድንበር በግልፅ ባለመካለሉ ምክንያት የአቢዬ ክልል በሁለቱም ወገኖች የይገባኛል ጥያቄ ይነሳበታል። ውዝግቡ እስኪፈታም በሁለቱም ሀገራት የተመረጡ ባለስልጣናትን ያካተተ ልዩ ቡድን አካባቢውን ሲያስተዳድር ቆይቷል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG