በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኮንጎ በደረሰ የጀልባ ስጥመት ስድስት ሰዎች ሞቱ


በምሥራቅ ኮንጎ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ በሚገኘው ኪቩ ሐይቅ፣ በተከሠተ አደገኛ ነፋስ ምክንያት፣ አንድ ጀልባ ሰጥሞ፣ ስድስት ሰዎች ሲሞቱ፣ ሌሎች በደርዘን የሚቆጠሩትን ማፈላለጉ ደግሞ ቀጥሏል፤ ሲሉ ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።

ጀልባዋ፣ ነጋዴዎችንና ዕቃቸውን ጭና ከሙጎቴ፣ የደቡብ ኪቩ መዲና ወደኾነቸው ጎማ በማቅናት ላይ እንደነበረች ታውቋል።

ጀልባዋ፣ 20 ኪ.ሜ. ከተጓዘች በኋላ፣ በአደገኛ ነፋስ ሁከት ገጥሟት ለመገልበጥ እንደበቃች፣ የሙጎቴ ፖሊስ ሓላፊን ጠቅሶ ኤኤፍፒ ዘግቧል።

የደቡብ ኪቩ አንድ ባለሥልጣን በበኩላቸው፣ ጀልባዋ 150 መንገደኞችን ይዛ እንደነበርና 80 ሰዎች ከአደጋው መትረፋቸውን አስታውቀዋል። የሦስት ሴቶች እና የሦስት ልጆች አስከሬን መገኘቱንም አክለዋል።

በኮንጎ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ፣ ለመጓጓዣ የሚያገለግሉ የየብስ መንገዶች ውስን በመኾናቸው፣ ሰዎች፣ በሐይቅ እና በወንዞች ላይ ለመጓዝ ስለሚገደዱ፣ “የጀልባ መስጠም አደጋ የተለመደ ነው፤” ተብሏል።

XS
SM
MD
LG