ዋሺንግተን ዲሲ —
አቶ ሲራጅ ፈጌሳ ከደኢህዴን ምክትል ሊቀመንበርነት መልቀቃቸውን የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ገለፀ።
የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢህዴን) ምክትል ሊቀመንበር አቶ ሲራጅ ፈጌሳ ከምክትል ሊቀመንበርነታቸው መነሳት እንደሚፈልጉ ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት ድርጅቱ ስለተቀበላቸው እንደለቀቁ ተገልጿል።
አቶ ሲራጅ የፌደራል ትራንስፖርት ባለሥልጣን ሚኒስትር ዴኤታ በአቶ ሚሊዮን ማቴዎስ እንደተተኩ ታውቋል።
ትናንት የድርጅቱ ሊቀመንበር አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ለቅቀው በቦታቸው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔዋ ወ/ሮ ሙፈርያት ካሚል መተካታቸው ይታወቃል፡፡
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ