በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“ሙዚቃ ከጭንቀት ታድጎናል” ትውልደ ኢትዮጵያ ዩክሬናውያን እህትማማች ድምጻውያን በጀርመን


“ሙዚቃ ከጭንቀት ታድጎናል” ትውልደ ኢትዮጵያ ዩክሬናውያን እህትማማች ድምጻውያን በጀርመን
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:26 0:00

“ሙዚቃ ከጭንቀት ታድጎናል” ትውልደ ኢትዮጵያ ዩክሬናውያን እህትማማች ድምጻውያን በጀርመን

"ፎ ሾ" FO SHO ዩክሬይን ተወልደው ባደጉ ሦስት ትውልደ ኢትዮጵያ እህትማማቾች የተመሠረተ የሙዚቃ ቡድን መጠሪያ ነው።

የቤተ እስራኤላውያን መሠረት ያላቸው እህትማማቾች መኖሪያቸው ከነበረችው ከሩስያ ጋራ የምትዋሰን የዩክሬይን በሃርከፍ ከተማ ከሁለት ዓመታት በፊት ሩሲያ የከፈተችውን ወረራ ሽሽተው ከቤተሰቦቻቸው ጋር፣ መጀመሪያ ወደ ፖላንድ ከተሻገሩ በኋላ፣ አሁን በጀርመኗ ሽቱትጋርት በስደት ላይ ይገኛሉ፡፡

በተዐምር ተርፈን በመጨረሻዋ ባቡር ለመውጣት ችለናል”

ጀርመን ከምትገኘው ባልደረባችን ሳራ ፍስሃዬ ጋር ቆይታ ያደረጉት ቤተልሔም መሪያም እና ጽዮና “ሙዚቃ ስደት ከሚያሳድረው ጭንቀት ታድጎናል” ብለዋል፡፡

በቀድሞዋ ሶቭየት ኅብረት ባገኙት የከፍተኛ ትምህርት ዕድል፣ ከኢትዮጵያ ወደ ዩክሬን አምርተው ሀርከቭ ውስጥ የኖሩት ወላጆቻቸው ከ30 ዓመት በላይ በሕክምና ሞያ ላይ ተሰማርተው የነበሩ ሲሆን ከሩሲያ ወረራ “በተዐምር ተርፈን በመጨረሻዋ ባቡር ለመውጣት ችለናል” ብለዋታል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG