በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሲንጋፖር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፕዮንግያንግን ይጎበኛሉ

ሲንጋፖር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርዋ በያዝነው ሳምንት ፕዮንግያንግን እንደሚጎበኙ ገልፃለች። ከተማይቱ በከፍተኛ ደረጃ የሚጠበቀውን የሰሜን ኮርያና የዩናይትድስ ስቴትስ መሪዎች ስብሰባን ከምታስተናግድበት ጥቂት ቀናት በፊት ማለት ነው።

ሲንጋፖር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርዋ በያዝነው ሳምንት ፕዮንግያንግን እንደሚጎበኙ ገልፃለች። ከተማይቱ በከፍተኛ ደረጃ የሚጠበቀውን የሰሜን ኮርያና የዩናይትድስ ስቴትስ መሪዎች ስብሰባን ከምታስተናግድበት ጥቂት ቀናት በፊት ማለት ነው።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቪቪያን ባላክሪሽናን ሀሙስና አርብ በሰሜን ኮርያ ቆይታ የማድረግ ዕቅድ አላቸው። ሲንጋፖር ከዩናይትይድ ስቴትስና ከሰሜን ኮርያ ጋር ዲፕሎማስያዊ ግንኙነት አላት።

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕና የሰሜን ኮርያው መሪ ኪም ዦንግ ኡን በመጪው ሳምንት ማክሰኞ በሲንጋፖር እንዲገናኙ ይጠበቃል። ስብሰባው ሴነቶስ በተባለው ደሴት በሚገኝ ካፔላ ሆቴል እንደሚካሄድ የዋይት ሃውስ ቤተ-መንግስት ገልጿል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG