በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ግብፅ መስጊድ ላይ በደረሰ ጥቃት 235 ሰዎች ተገደሉ


ኤል ራውዳ መስጊድ
ኤል ራውዳ መስጊድ

ግብፅ በታወከው ሰሜናዊ ሲናይ በረሃ በሚገኝ ሕዝብ የበዛበት መስጊድ ተጠርጣሪ ታጣቂዎች ሁለት መቶ ሰላሳ አምስት ሰዎች መግደላቸውን የፀጥታ ባለሥልጣናት መናገራቸውን የመንግሥቱ ዜና ማሰራጫዎች አስታወቁ።

ግብፅ በታወከው ሰሜናዊ ሲናይ በረሃ በሚገኝ ሕዝብ የበዛበት መስጊድ ተጠርጣሪ ታጣቂዎች ሁለት መቶ ሰላሳ አምስት ሰዎች መግደላቸውን የፀጥታ ባለሥልጣናት መናገራቸውን የመንግሥቱ ዜና ማሰራጫዎች አስታወቁ።

ፅንፈኞች ከክፍለ ሀገሩ ዋና ከተማ ከኤል ሪሽ ወጣ ብሎ በሚገኝ ቢር አል አቤድ በሚባል ከተማ የሚገኘውን ኤል ራውዳ መስጊድ ዒላማ ያደረገ ጥቃት ማካሄዳቸውን ባለሥልጣናቱ ገልፀዋል ማለታቸውን ነው የግብፁ የመንግሥት የዜና አገልግሎት ሜና የዘገበው።

በአራት መኪናዎች ሆነው የደረሱት ታጣቂዎች ዛሬ ጁምዓ ፀሎት ላይ በነበሩ ምዕመናን ላይ ተኩስ እንደከፈቱ ባለልሥልጣናቱ አመልክተዋል። የዓይን ምስክሮች በበኩላቸው አምቡላንሶች

የጥቃቱን ሰለባዎች ወደአቅራቢያ ሆስፒታሎች ሲወስዱ ማየታቸውን ገልፀዋል።

አጎራባች እስራኤል ለግብፅ የሃዘን መግለጫ አስተላልፋለች።

የግብፅ የፀጥታ ኃይሎች በተለይ በሰሜኑ ሲናይ አካባቢ “የእስልምና መንግሥት” ብሎ ራሱን ከሚጠራው ቡድን ጋር እየተዋጉ ናቸው። ባለፉት ሦስት ዓመታት ውስጥ ውጊያው ከተባባሰ ወዲህ ታጣቂዎች ብዙ መቶ ፖሊሶችና ወታደሮች ገድለዋል።

የፀጥታ ኃይሎችን ዒላማ የሚያደርጉት ነውጠኞቹ ከሲናይ ውጭ በተለያዩ የግብፅ አካባቢዎች አብያተ ክርስቲያናት እና ሲቪሎች ላይ ጥቃት ያደርሳሉ፡፡

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG