ዋሺንግተን ዲሲ —
ጁሊስ ማዳ ባዮ በጣም የተቀራረብ የፕሬዚዳንት ማጣርያ ምርጫ ካሸነፉ በኋላ ዛሬ ቃለ መሃላ ፈፅሟል።
ባዮ ትላንት ከእኩለ ሌሊት በፊት ቃለ መሃላ የፈፀሙት የሀገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን ባለፈው ቅዳሜ በተካሄደው ምርጫ ማሸነፋቸውን ካስታወቀ በኋላ ነው። ወታደራዊ ኃላፊ የነበሩት የሲየራልዮን ህዝባዊ ፓርቲ መሪ ባዮ ያሸነፉት ወደ 52 ከመቶ በሚጠጋ ድምፁ ነው። በውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ያገለገሉት የመላ ህዝብ ኮንግረስ ፓርቲ መሪ ሳሙራ ዊልሰን ካማራ ያገኙት ድምፅ ከ48 ከመቶ በላይ ነው።
የፈረንሳይ የዜና አገልግሎት አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ በዘገበው መሰረት 3.1 ሚልዮን የሚሆን ህዝብ በምርጫው ተሳትፏል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ