ሀዋሳ —
ሲዳማ 10ኛው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ሆኖ እንዲደራጅና ህግ መንግሥታዊ መብቱን ያስከበረው በለውጡ መንግሥት የተተገበረው እውነተኛ የፌዴራልዝም ሥርዓት መሆኑን የሃዋሳ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነ ተናገሩ።
የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ርስቱ ይርዳው በበኩላቸው ለሲዳማ ህዝብ ደስታቸውን ገልፀው በክልሉ በአያልው የሚነሱ የክልል ጥያቄ በተመለከተ “አንደኛውን እግር እዚጋ ሌላኛው ሌላ ቦታ ያደረጉ ፤ የፖሊቲካ ትርፍ ለማግኘት የሚሯሯጡ አካላትን መከተልና ትናንት የህዝቦችን መብት አፍኖ ካቆየው ሥርዓት ጎን መቆም ኪሳራ እንጂ ትርፍ የለውም” ብለዋል።
የደቡብ ክልልን በአዳዲስ ክልሎች ለማደራጀት የተጀመረው ውይይት ገና ያልተጠናቀቀ መሆኑን የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ ጥላሁን ከበደ አስታውቀዋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።