በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሲዳማ ክልል በሰብዓዊ መብቶች ጥሰት የተጠረጠሩ ፖሊሶች ተባረሩ


በሲዳማ ክልል በሰብዓዊ መብቶች ጥሰት የተጠረጠሩ ፖሊሶች ተባረሩ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:36 0:00

በሲዳማ ክልል በሰብዓዊ መብቶች ጥሰት የተጠረጠሩ ፖሊሶች ተባረሩ

“የዜጎችን ሕጋዊ እና ሰብዓዊ መብቶች ጥሰዋል”፤ ያላቸውን 157 የፖሊስ አባላት እና አዛዦች፣ ከሥራ ማሰናበቱን፣ የሲዳማ ክልል ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ አስታወቀ።

ከተባረሩት መካከል 27ቱ፣ በሕግ እንደሚጠየቁና ሌሎች 305 አባላት ደግሞ፣ ከባድ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው፣ የቢሮው ኃላፊ አቶ ዓለማየሁ ጢሞቴዎስ፣ ለአሜሪካ ድምፅ ገልጸዋል።

ከሥራ መባረራቸው የተገለጸው የፖሊስ አባላት፣ ከሳጂን እስከ ኢንስፔክተር እና የወረዳ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት አዛዥ ደረጃ ድረስ የሚገኙ ሲኾኑ፤ ምርመራው የተደረገባቸውም፣ ባለፈው አንድ ወር ውስጥ እንደኾነ፣ የክልሉ ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ሓላፊ አስታውቀዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያድምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG