በአንዳንድ የኦሮምያ እና የሲዳማ ክልል አዋሳኝ አከባቢዎች የሰው ሕይወት የጠፋበት ግጭት መፈጠሩን የገለፀው የሲዳማ አንድነት ፓርቲ - ፌዴራል መንግሥት መፍትሔ እንዲፈልግና ግጭቱን በአፋጣኝ እንዲያስቆም ጥሪ አቅርቧል።
በሰሞኑ ግጭት ሰባት ሰዎች መገዳላቸውንና 17 መቁሰላቸውንም ፓርቲው ትናንት በሃዋሳ ከተማ ለጋዜጠኞች በሰጠው መግለጫ አስታውቋል። ችግሩ ሁለቱ ሕዝቦች ባሏቸዉ ባሕላዊ የግጭት መፍቻ ዘዴዎች ሊቀረፍ እንደሚችልም ጠቅሷል።
ግጭቱን በተመለከተ ከሲዳማ እና ከኦሮሚያ ክልል መንግሥታት የተሰጠ መግለጫም ሆነ አስተያየት ባይኖርም - የፓርቲውን መግለጫ የሃዋሳው ዘጋቢያችን ዮናታን ዘብዴዎስ ተከታትሎታል።
የፕሮግራሙ ተከታታይ ክፍሎች
-
ሴፕቴምበር 16, 2024
የምስራቅ አፍሪካ የልማት በየነ መንግስታት (ኢጋድ) ዋና ጸሃፊ ሶማሊያን ጎበኙ
-
ሴፕቴምበር 14, 2024
የኢትዮጵያውያን ክለቦች ግጥሚያ በዋሽንግተን ዲሲ
-
ሴፕቴምበር 13, 2024
“በትግራይ ወደ ጦርነት ለመመለስ ምንም ዓይነት ምክንያት መኖር የለበትም” ዩናይትድ ስቴትስ
-
ሴፕቴምበር 13, 2024
ከዱራሜ እስከ ዋሽንግተን - የመጀመሪያዋ ኢትዮጵያዊ ሴት ፕሮፌሽናል እግር ኳስ ተጫዋች ሎዛ አበራ
-
ሴፕቴምበር 11, 2024
2016 ለኢትዮጵያውያን እንደምን አለፈ? መጭውስ 2017 ምን ይዞ ይሆን?