በአንዳንድ የኦሮምያ እና የሲዳማ ክልል አዋሳኝ አከባቢዎች የሰው ሕይወት የጠፋበት ግጭት መፈጠሩን የገለፀው የሲዳማ አንድነት ፓርቲ - ፌዴራል መንግሥት መፍትሔ እንዲፈልግና ግጭቱን በአፋጣኝ እንዲያስቆም ጥሪ አቅርቧል።
በሰሞኑ ግጭት ሰባት ሰዎች መገዳላቸውንና 17 መቁሰላቸውንም ፓርቲው ትናንት በሃዋሳ ከተማ ለጋዜጠኞች በሰጠው መግለጫ አስታውቋል። ችግሩ ሁለቱ ሕዝቦች ባሏቸዉ ባሕላዊ የግጭት መፍቻ ዘዴዎች ሊቀረፍ እንደሚችልም ጠቅሷል።
ግጭቱን በተመለከተ ከሲዳማ እና ከኦሮሚያ ክልል መንግሥታት የተሰጠ መግለጫም ሆነ አስተያየት ባይኖርም - የፓርቲውን መግለጫ የሃዋሳው ዘጋቢያችን ዮናታን ዘብዴዎስ ተከታትሎታል።
የፕሮግራሙ ተከታታይ ክፍሎች
-
ማርች 14, 2025በአፍሪካ የኅይል አቅርቦት ላይ ያተኮረውና በዋሽንግተን ዲሲ የተካሔደው ጉባኤ
-
ማርች 14, 2025የኢትዮጵያውያት ሴቶች ጥያቄ ምንድን ነው? - የአድማጭ ተመልካቾች አስተያየት
-
ማርች 13, 2025አርቲስት አንዱዓለም ጎሣ ተጨማሪ 13 ቀናትን በእስር እንዲቆይ ፍርድ ቤት ፈቀደ
-
ማርች 13, 2025ሩሲያ የተቆጣጠረቻቸውን የዩክሬን ግዛቶች እንደያዘች መቀጠል ትሻለች