በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጽ/ቤቱ መመዝበሩንና አባላቱም መታሰራቸውን የገለጸው የሲዳማ ፌዴራሊስት ፓርቲ ክልሉን ወቀሰ

ጽ/ቤቱ መመዝበሩንና አባላቱም መታሰራቸውን የገለጸው የሲዳማ ፌዴራሊስት ፓርቲ ክልሉን ወቀሰ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:26 0:00

ጽ/ቤቱ መመዝበሩንና አባላቱም መታሰራቸውን የገለጸው የሲዳማ ፌዴራሊስት ፓርቲ ክልሉን ወቀሰ

በሐዋሳ ከተማ የሚገኘው የሲዳማ ፌደራሊስት ፓርቲ ዋና ጽሕፈት ቤት፣ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች መሰበሩን፣ የፓርቲው መረጃዎች መወሰዳቸውንና አመራሮቹ እና አባላቱ መታሰራቸውን፣ የጽ/ቤቱ ሓላፊ ሓላፊ አቶ ገነነ ሐሳና ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

የክልሉ የመንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ ጉዳዮች ቢሮ ሓላፊ አቶ ወሰንየለህ ስምዖን፣ በፓርቲው አመራሮች መካከል ባለ የእርስ በርስ ሽኩቻ እንጂ፣ በክልሉ መንግሥት ላይ የሚቀርበው ክስ እና ወቀሳ፣ መሠረተ ቢስ ውንጀላ ነው፤ ሲሉ፣ የፓርቲውን ክስ አጣጥለዋል።

ሰዎቹ የታሰሩትም፣ በሕግ ጥሰት ተጠርጥረው እንጂ፣ በፖለቲካ አቋማቸው እንዳልኾነም፣ ሓላፊው አክለው ተናግረዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG