በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የሚገኙ ተማሪዎች ከሁለት ወራት የክረምት እረፍት በኋላ አዲሱን የ2015 የትምህርት ዘመን ትናንት ሰኞ ጀምረዋል።
ለዓመቱ ትምህርት በ34 ሺህ ትምህርት ቤቶች ከ16 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች መመዝገባቸውን የትምህርት ሚኒስቴር መረጃ አመልክቷል።
በሌላም በኩል በፀጥታ ችግር፣ በድርቅ እና በጎርፍ ምክንያት በኢትዮጵያ የሚገኙ ወደ 3 ሚሊዮን የሚጠጉ ታዳጊዎች ከትምህርት ገበታ ውጭ እንደሆኑ ባለፈው ሰኔ ይፋ የተደረገ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሪፖርት አመልክቷል።
አምና በዚህ ሰዓት የጦርነት ቀጠና ከነበሩት አካባቢዎች ውስጥ ዘንድሮ ወደ ሰላማዊ ሁኔታ የተመለሱና የ2015ትን የትምህርት ዘመን ከቀረው የአገሪቱ ክፍል ጋር የጀመሩም አሉ። የደሴ ከተማ ከነዚህ አካባቢዎች አንዷ ናት።
[ሙሉውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ]