ዋሺንግተን ዲሲ —
በአፍጋኒስታን ደቡባዊ ግዛት በምትገኘው የካንዳኻር ከተማ በሺአ መስጊድ ውስጥ በደረሰ የቦንብ ፍንዳታ፣ በዓርብ ጸሎት ላይ የነበሩ 16 ሰዎች ሲሞቱ ከ50 በላይ የሚሆኑት ደግሞ ቆስለዋል፡፡
የታሊባን ቃል አቀባይ ቢላል ካሪሚ ለቪኦኤ እንዳስታወቁት በካንዳሃር የደረሰው የቦምብ ፍንዳታ በርካታ ሰዎችን መግደልና ማቁሰሉን ገልጸው ለፍንዳታው ተጠያቂ የሆኑ ወገኖች ወደ ፍርድ ለማምጣት ምርመራ እየተካሄደ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ለአደጋው ኃላፊነቱን የወሰደ ወገን እስካሁን የለም፡፡
ባለፈው ዓርብም በሰሜን ምስራቃዊ አፍጋኒስታን ከተማ ኩንዱዝ ውስጥ በሚገኝ የሺአ መስጊድ ውስጥ በደረሰ የቦምብ ፍንዳታ ቢያንስ ከ50 ሰዎች በላይ ሲሞቱ ሌሎች በርካቶች ቆስለዋል፡፡
ለዚያ ጥቃት ኃላፊነቱን የወሰደው የእስላማዊ መንግሥት ኮሆራሳን (አይኤስ ኮሆራሳን) በመባል የሚታወቀውና ከእስላማዊ መንግስት ቡድን አራማጆች ጋር ግንኙንት ያለው ድርጅት መሆኑ ይታወሳል፡፡