በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የመን ጠረፍ አካባቢ በነበረ መርከብ ላይ ጥቃት ደረሰ


ፎቶ ፋይል፦ የመን ካርታ
ፎቶ ፋይል፦ የመን ካርታ

በየመን ደቡባዊ የባሕር ጠረፍ ላይ ይጓዝ የነበረ መርከብ ጥቃት እንደደረሰበት የብሪታኒያ የንግድ መርከብ ድርጅት ተናገረ።

ለንግድ መርከቦች የደህንነት ማስጠንቀቂያ የሚሰጠው ድርጅት በየመን ጠረፍ ላይ ማንነታቸው ባልታወቀ መርከቦች ላይ ጥቃት መሰንዘሩን መረጃ እንደደረሰው አስታውቋል።

ጥቃቱን ያደረሱት እያንዳንዳቸው ቢያንስ አራት ሰዎች የያዙ ሶስት ጀልባዎች መሆናቸውን ድርጅቱ አመልክቷል። ሌላ ዝርዝር መረጃ አልሰጠም። በተጠቀሰው አካባቢ መርከቦች ላይ ጥቃት በማድረስ ቀደም ሲል የሚወነጀሉት የሶማሊያ የባህር ላይ ዘራፊዎች እንደነበሩ ይታወሳል።

በቅርብ ዐመታት ደግሞ በጠረፉ አካባቢ በመርከቦች ላይ የሚደርሰው ጥቃት መነሾ ላለፉት ስምንት ዐመታት ከቀጠለው የየመን የእርስ በርስ ጦርነት ጋር የተያያዘ መሆኑ ተነግሯል።

XS
SM
MD
LG