ወደ ዋግኽምራ የሚገቡ ተፈናቃዮች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ዞኑ አስታወቀ
በህወሓት ቁጥጥር ሥር ናቸው ከተባሉ አካባቢዎች ተፈናቅለው ወደ ዋግኽምራ ዞን ሰቆጣ ከተማ የሚገቡ ተፈናቃዮች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን የዞኑ ኮሚኒኬሽን መምሪያ ገለፀ። በከተማው በአሁኑ ሰዓት ከ70 ሺ በላይ ተፈናቃይ እንዳለ የገለፁት መምሪያ ኃላፊው አቶ ከፍያለው ደበሽ በየቀኑ ቁጥሩ እስከ 200 የሚደርሱ ተፈናቃዮች ወደ ከተማው እየገቡ መሆኑን ተናግረዋል። ተፈናቃዮቹ በአካባቢው የሚበላ ነገር አለመኖሩንም ለመፈናቀላቸው ምክኒያት እንደሆናቸው ተናግረዋል።
የፕሮግራሙ ተከታታይ ክፍሎች
-
ጁን 28, 2022
የናይጄሪያ ቤተክርስቲያናት ከጥቃቱ በኋላ ጥበቃቸውን አጠናክረዋል
-
ጁን 27, 2022
የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፅንስ ማቋረጥ ህገ መንግሥታዊ መብት ሻረ
-
ጁን 27, 2022
የዝንጀሮ ፈንጣጣ ምንድነው?
-
ጁን 27, 2022
ኢትዮጵያ 7 የተማረኩ ወታደሮችና አንድ ሲቪል ገላብኛለች ስትል ሱዳን ከሰሰች