በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

መስከረም አንድ በአሜሪካ

ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

መስከረም አንድ በአሜሪካዊያን ዘንድ በከበደ ኀዘን ታስቦ የሚውል ቀን ነው። ልክ የዛሬ 16 ዓመት መስከረም 1994 ዓ.ም. በበረራ ቁጥር 77 የተመዘገበ የአሜሪካን ኤይርላይንስ አይሮፕላን ተሣፍረውበት ከነበሩ 59 መንገደኞች ጋር ተጠልፎ የዩናይትድ ስቴትስ የመከለከያ ሚኒስቴርን መታ። ያኔ ፔንታገን ውስጥ የነበሩ 125 ሰዎች ተገደሉ።

ከዚያ ቀደም ሲል በአል ቃይዳ ሰዎች የተጠለፈ የመጀመሪያው አይሮፕላን ከጠዋቱ ለሦስት ሰዓት ሃያ ደቂቃ ጉዳይ ኒው ዮርክ ከሚገኙት ሁለት ሰማይ ጠቀስ መንታ ፎቆች ከአንዱ ጋር ተጋጨ፤ ከሃያ ሦስት ደቂቃዎች በኋላም ሁለተኛው መንታ ሕንፃ ተመታ። ግዙፎቹ የዓለም ንግድ ማዕከል ፎቆች ወደቁ።

አራተኛው አይሮፕላን ፔንሲልቬንያ ግዛት ውስጥ በተሣፋሪዎቹና በጠላፊዎቹ መካከል በተነሣው ትንቅንቅ መሃል ወደቀ።

በመስከረም አንዱ ጥቃት የ2996 ሰው ሕይወት ጠፍቷል። በስድስት ሺህ ሰው ላይ ጉዳት ደርሷል። አሥር ቢሊዮን ዶላር የተገመተ ንብረት ወድሟል።

ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ‑ኢትዮጵያ አሜሪካዊያን ዕለቱን በተደባለቀ መንፈስ ይውሉታል። አንድም በአዲስ ዓመት ስሜት፤ አንድም በሽብሩ ጥቃት የኀዘን መንፈስ።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

መስከረም አንድ በአሜሪካ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:55 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG