በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የመስከረም 1-94 ሽብር ዝክር ባሜሪካ


ዩናይትድ ስቴትስ የሽብር ጥቃት የተፈፀመባትን ሃያኛ ዓመት መታሰቢያ ፕሬዚዳንቷ ዛሬ በሦስት የተለያዩ ሥፍራዎች እየተገኙ እየዘከሩ ናቸው። በቅርብ የታሪክ ትውስታ በክፋቱ እጅግ የበረታ እንደሆነ የሚነገርለት ይህ ጥቃት በፀጥታና በፅሞና እየተከናወኑ ባሉ ተግባራት ነው።

ፕሬዚዳንቱ የመጀመሪያዎቹ ጥቃቶች በመንትያ ህንፃዎቹ ላይ በተፈፀሙባት ኒው ዮርክ ከተማ ዛሬ ሲገኙ የተጠናከረ የፀጥታ ጥበቃ የነበረ ቢሆንም አስጊ ሁኔታ ሊኖር ስለመቻሉ አንዳችም መረጃ እንደሌላቸው ከንቲባዋ ቢል ደ ብላሲዮ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።

ፕሬዚዳንቱ ከቀድሚት እመቤት ጋር ሆነው በተገኙባቸው የኒው ዮርክ የዓለም የንግድ ማዕከልና በፔንሲልቬንያው የሻንክስቪል 93 ብሄራዊ መዘክር የአበባ ጉንጉኖችን ያኖሩ ሲሆን በመቀጠልም ወደ ዋሺንግተን ተመልሰው የጥቃቱ አንደኛው ዒላማ በነበረው በመከላከያ መሥሪያ ቤቱ ፔንታገን አበባ እንደሚያኖሩ የዛሬ መርኃግብራቸው ያሳያል።

የዘጠና በላይ ሃገሮች ዜጎች የሆኑ 2977 ሰዎች የተገደሉበትንና ብዙዎች የቆሰሉበት ይህ የሽብር አድራጎት የተፈፀመበትን ዕለት የሰውን ልጅ አዕምሮ ያቆሰለ እጅግ አሳዛኝ ቀን ሲሉ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬሽ ጠርተውታ። ዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ከሽብር ነፃ የሆነ ዓለም ለመፍጠር በሚደረገው ርብርብ ውስጥ ብርታት፣ ጥንካሬና አንድነት እንዲኖረው ጠይቀዋል።

የመስከረም 1-94 ሽብር ዝክር ባሜሪካ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:47 0:00


XS
SM
MD
LG