በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ራሣቸውን እንዳጠፉ የተጠረጠረው የሶል ከንቲባ አስከሬን ተገኘ


የደቡብ ኮሪያ ዋና ከተማ የሶል ከንቲባ ዛሬ ማለዳ አስከሬናቸው መገኘቱን የሀገሪቱ ፖሊስ አስታውቋል፤ ራሳቸው ህይወታቸውን አጥፍተው ነው ተብሎ ተጠርጥሯል።

የሥድሳ አራት ዓመቱ የሶል ከንቲባ ፓርክ ዎን ሱን ከትናንት ሃሙስ ጀምሮ የደረሱበት ጠፍቷል የሚል ሪፖርት ደርሶት እንደነበር የገለጸው ፖሊስ ከእኩለ ሌሊት በኋላ አንድ ተራራ ዳር እስከሬናቸው ትገኝቷል ብለዋል።

ከንቲባውን ከመጥፋታቸው ከአንድ ቀን በፊት የቀድሞ ፀሃፊያቸው የነበሩ ሴት ወሲባዊ ወከባ አድርሰውብኛል ብለው ውንጀላ አሰምተው እንደነበር ተገልጿል።

ሟቹ በተለይም ቤተሰባቸውና ሌሎችም ይቅርታ የጠየቁበት ደብዳቤ ቤታቸው እንደተገኘ ታውቋል።

XS
SM
MD
LG