ዋሺንግተን ዲሲ —
በቅርቡ ለተመልካቾች ማክሰኞ ምሽት የተዋወቀ ተከታታይ የቴሌቭዥን ድራማ ነው - ሰንሰለት።
ታዋቂና አዳዲስ ተዋናዮች የተሳተፉበትና ቀጣይ ነውና ወደፊትም የሚሳተፉበት፤ የሁለት ዓለም ሕይወት ሊያስተሳስር የታለመ ድራማ ነው።
በዩናይትድ ስቴትስ ተሰርቶ ወደ ኢትዮጵያ ሲሰራጭ የመጀመሪያው እንደሚሆን የተነገረለት የተከታታይ ፊልም ሥራ የራሱን ታሪክ የጻፈም ይመስላል።
ከዋሽንግተን ዲሲ ወጣ ብላ በምትገኘው የሲልቨርስፕሪንግ ከተማ በይፋ የተዋወቀበትን ሥነ ሥርዓት ተንተርሶ የተሰናዳ ዘገባ ቀዳሚው ነው።
የሙዚቃና የድምፅና የምስል አቀናባሪዎችንና ሌሎች አጋዥ የፊልም ሞያተኞችን ጨምሮ ከሠላሳ በላይ ሰዎች የተሳተፉበት ተከታታይ የቴሌቭዥን ድራማ ደራሲና ዳይሬክተር ተመስገን አፈወርቅ እና እንዲሁም ሌላው የፊልሙ ዳይሬክተር ቴዎድሮስ ለገሰ ጋር ያደረግነው ቆይታ ምጥን የመጀመሪያ ክፍልም ዘገባውን ይከተላል።
የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ