በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሳዑዲ ልዑክ በአስመራ


የሳዑዲ አረብያ ልዑክ በአስመራ
የሳዑዲ አረብያ ልዑክ በአስመራ

በሌተናንት ጀኔራል ልዑል ፋሐድ ቢን ቱርኪ ቢን አብዱልዐዚዝ የሚመራ ከፍተኛ የሳዑዲ አረብያ ልዑክ ትላንት አስመራ ገብቷል፡፡

በሌተናንት ጀኔራል ልዑል ፋሐድ ቢን ቱርኪ ቢን አብዱልዐዚዝ የሚመራ ከፍተኛ የሳዑዲ አረብያ ልዑክ ትላንት አስመራ ላይ ከፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ተገናኝቶ ስለቀይ ባህር ቀጠና ፀጥታ ጉዳይ መነጋገራቸውን ሻዕባይት የተባለው የኤርትራ መንግሥት ድረ- ገፅ ገልጿል። ልዑሉ ፀረ አሸባሪነት የተባለው የጥምረት ኃይሎች አዛዥ ናቸው።

የኤርትራ ሚድያ ስብሰባው የኤርትራንና የሳዑዲ አረብያን የጋራ ግንኙነት በማዳበርና በቀይ ባህር ቀጠና ፀጥታ ጉዳይ ላይ ያተኮረ ነበር ከማለት በስተቀር የሰጠው ዝርዝር መግለጫ የለም።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG