በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሴኔጋል ሁለት ቀዳማዊ እመቤቶች ይኖሯታል


የሴኔጋል ፕሬዝደንታዊ ምርጫ አሸናፊ የሆኑት ባሲሩ ፋይ ከመጀመሪያ ሚስታቸው ማሪ ኮኔ እና ሁለተኛ ሚስታቸውን አብሳ ፋዬ ጋር እአአ መጋቢት 24/2024
የሴኔጋል ፕሬዝደንታዊ ምርጫ አሸናፊ የሆኑት ባሲሩ ፋይ ከመጀመሪያ ሚስታቸው ማሪ ኮኔ እና ሁለተኛ ሚስታቸውን አብሳ ፋዬ ጋር እአአ መጋቢት 24/2024

በቅርቡ የሴኔጋል ፕሬዝደንታዊ ምርጫ አሸናፊ የሆኑት ባሲሩ ፋይ የምርጫ ዘመቻቸውን ባጠናቀቁበት መድረክ ላይ የሁለቱንም ሚስቶቻቸውን እጅ ይዘው ብቅ ብለዋል።

የተመራጩ ፕሬዝዳንት ድርጊት ከዚህ በፊት ያልታየ እና በአገሪቱ የተለመደው የወንዶች ከአንድ በላይ የትዳር አጋር መያዝ ነውር እንዳልሆነ ለማሳየት የተጠቀሙበት ነው ተብሏል።

በአብዛኛው የእስልምና እምነት ተከታዮች ባሏት ሴኔጋል የወንዶች ከአንድ በላይ የትዳር አጋር መያዝ በሰፊው የተለመደ ነው።

ተመራጩ ፕሬዝደንት ባሲሩ ፋይ ከመጀመሪያ ሚስታቸው ማሪ ኮኔ ጋር ለ15 ዓመታት በትዳር የቆዩ ሲሆን፣ አራት ልጆችም አሏቸው። ማሪ ኮኔ በሕዝብ ፊት ሲቀርቡ የመጀመሪያ ግዜያቸው ነው። ሁለተኛ ሚስታቸውን አብሳ ያገቡት ደግሞ ከአንድ ዓመት ጥቂት ቀደም ብሎ ነው።

ጂቢ ዲያካቴ የተባሉ የሕብረተሰብ ጥናት ባለሙያ፣ ድርጊቱ “በአገሪቱ ያለውን የወንዶች ከአንድ በላይ የትዳር አጋር የመያዝ ልምድ እውቅና የሰጠና በሴኔጋል ያለውን እውነታ ያሳየ ነው” ሲሉ ለኤኤፍፒ የዜና ወኪል አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

“ሁለተኛ ሚስት መሆኔ የመጀመሪያ ሚስት ከመሆን ይልቅ ይስማማኛል” ስትልም በአገሪቱ ታዋቂ ዘፋኝ የሆነችው ሚያ ጊሴ በቅርቡ በማሕበራዊ መድረክ በኩራት ተናግራለች፡፡

“ከአንድ በላይ የትዳር አጋር መያዝ የተመሳሳይ ፆታ አጋር ከመያዝ ጋራ ፉክክር ውስጥ ናቸው፣ ምዕራቡ ዓለም የእኛን ባህል ሊተች አይችልም” ሲሉ ሌላው ታዋቂ የማሕበረሰብ ጥናት ባለሙያ የሆኑት ፋቱ ሳር ለኤኤፍፒ ተናግረዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG