በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሴኔጋል ፓስተር ኢንስቲቲዩት የ50 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ተፈቀደለት


የጤና ሰራተኛዋ የኮቪድ-19 ክትባት ለመስጠት እየተዘጋጁ በዳካር፤ ሴኔጋል
የጤና ሰራተኛዋ የኮቪድ-19 ክትባት ለመስጠት እየተዘጋጁ በዳካር፤ ሴኔጋል

የአፍሪካን የክትባት ምርት ለማሳደግ በተያዘ ጥረት የሴኔጋል ፓስተር ኢንስቲቲዩት የ50 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ማግኘቱ ተዘገበ፡፡

ለሴኔጋሉ የጤና ምርምር በቀጣዮቹ 10 ዓመታት የሚጠናቀቀውን የገንዘብ ድጋፍ የሚሰጠው የወረርሺኞች ዝግጁነት ጥምረት የተባለው ተቋም ሥምምነቱ መፈረሙን ትናንት ሀሙስ አስታውቋል፡፡

መቀመጫውን ኖርዌይ ያደረገው ዓለም አቀፍ ህብረት በታዳጊ ሀገሮች ክትባት አምራች ተቋማት በማቋቋም ላይ ሲሆን ዓላማውም ወደፊት ለሚሚከሰቱ ወረርሺኞች ተቀማጭ ክትባቶችን ለማዘጋጀት መሆኑ ተመልክቷል፡፡

ለሴኔጋሉ ፓስተር ኢንስቲቲዩት በቀጣዮቹ ሦስት ዓመታት የሚሰጠው የመጀመሪያው 15 ሚሊዮን ዶላር ማዕከሉ ለመደበኛ እና ለወረርሺኞች ክትባቶች ማምረቻዎችን ለመገንባት የሚውል መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

የኮቪድ 19 ዓለም አቀፍ ወረርሺኝ በተቀሰቀሰ ጊዜ አፍሪካ እንደሌሎቹ የዓለም ድሃ አካባቢዎች በቂ የክትባት አቅርቦት ያላገኘች ሲሆን ያም አህጉሪቱ የራሷን ክትባት ማምረት እንደሚኖርባት አጉልቶ ማሳየቱን ዘገባው አያይዞ አውስቷል፡፡

XS
SM
MD
LG