በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሴኔጋል ፕሬዚዳንት ከኮሮናቫይረስ ጋር በተያያዘ ራሳቸውን አገለሉ


ፎቶ ፋይል፦ የሴኔጋል ፕሬዚዳንት ማኪ ሳል
ፎቶ ፋይል፦ የሴኔጋል ፕሬዚዳንት ማኪ ሳል

የሴኔጋል ፕሬዚዳንት ማኪ ሳል በኮሮናቫይረስ ከተያዘ ሰው ጋር የነበራቸውን ንክኪ ተከትሎ ለጥንቃቄ ሲባል ራሳቸውን ለይተዋል።

የፕሬዚዳንቱ ጽ/ቤት ባወጣው መግለጫ ፕሬዚዳንቱ ተመርመረው ከቫይረሱ ነፃ መሆናቸው ተረጋጋጧል፤ ይሁን እንጂ በሃኪሞች ምክር መሰረት ለሁለት ሳምንት ተለይተው ይቀመጣሉ ብለዋል።

በተያያዘ ዜና ለቫይረሱ መጋለጣቸውን ትናንት ይፋ ያደረጉት የሴኔጋል ፓርላማ አባልዋ ዬዪ ዲያሎ ህዝቡ ቫይረሱን ለመከላከል የሚያሰፈጉትን አካላዊ ርቀት መጠበቅና ሌሎችም መንገዶች ሁሉ በመጠቀም ራሱን እንዲጠብቅ ተማፅነዋል።

ሴኒጋል ውስጥ እስካሁን በምርመራ የተረጋገጠው የቫይረሱ ተጋላጮች ቁጥር ከ6ሺህ 1መቶ መብለጡን የሞቱት ደግሞ 93 መድረሳቸውን ዜናው ጨምሮ አመልክቷል።

XS
SM
MD
LG