በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሴኔጋል ተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች ከእስር ተለቀቁ


የሴኔጋል ተቃዋሚ መሪ ኡስማኔ ሶንኮና ምክትላቸው ባሲሩ ፋዬ ከእስር ከተፈቱ በኋላ ደጋፊዎች የተሳፈሩበትን መኪና አጅበው፤ ዳካር፣ ሴኔጋል እአአ መጋቢት 15/2024
የሴኔጋል ተቃዋሚ መሪ ኡስማኔ ሶንኮና ምክትላቸው ባሲሩ ፋዬ ከእስር ከተፈቱ በኋላ ደጋፊዎች የተሳፈሩበትን መኪና አጅበው፤ ዳካር፣ ሴኔጋል እአአ መጋቢት 15/2024

የሴኔጋሉ ተቃዋሚ መሪ ኡስማኔ ሶንኮ እና ምክትላቸው ባሲሩ ፋዬ ትላንት ከእስር ተፈቱ። ተቃዋሚዎቹ ከእስር የተፈቱት ሴኔጋል ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ልታደርግ አስር ቀናት በቀረበት ወቅት ነው።

የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ማኪ ሳል ከሁለት ሳምንታት በፊት መደረግ የነበረበትን ምርጫ ለማስተላለፍ መሞከራቸውን ተከትሎ አገሪቱ የፖለቲካ ቀውስ ውስጥ ከርማ ነበር። የአገሪቱ ሕገ መንግሥታዊ ም/ቤት የመንግሥትን ሃሳብ በመሻር ምርጫው በመጪው እሁድ እንዲደረግ አዟል።

ሶንኮ በሚያሰሙት ዲስኩር ወጣት ድምፅ ሰጪዎችን ስለሚስቡ፣ የምርጫውን ሁኔታ ሊቀይር ይችላል ተብሏል። ላለፉት ሁለት ዓመታት ከመንግሥት ጋራ ፍጥጫ ውስጥ የከረሙት ሶንኮ፣ ከሐምሌ ወር ጀምሮ በእስር ላይ ነበሩ።

በእርሳቸው ላይ የተከፈተው ክስ ፣ የኢኮኖሚ እና ማኅበራዊ ችግር፣ ባለፉት ሦስት ዓመታት ውስጥ ሞትን ያስከተለ ተቃውሞ እንዲነሳ አድርጓል።

ሶንኮ ከእስር እንደሚለቀቁ ቀድመው ወሬውን የሰሙ በመዲናዋ ዳካር የሚገኙ ደጋፊዎቻቸው ደስታቸውን ለመግለፅ መንገድ ላይ ወጥተዋል።

ፕሬዚዳንት ማኪ ሳል በእሁዱ ምርጫ አይሳተፉም።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG